የአብክመ ዉሃና ኢነርጂ ቢሮ ሰራተኞችና አመራሮች የጎንደር ከተማ መጠጥ ዉሃ ፕሮጀክትን ጎበኙ

የጎንደር ከተማ ህብረተሰብን በዘላቂነት የንጹህ መጠጥ ዉሃ ተደራሽ ለማድረግ ከመገጭ መስኖ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ጋር አቀናጅት እየተሰራ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ይህ ፕሮጀክት የደረሰበትን ደረጃና አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ ለመመልከት የአብክመ ዉሃና ኢነርጂ ቢሮ ሰራተኞችና አመራሮች ጉብኝት አድገዋል፡፡ በዚህም መሰረት ፕሮጀክቱ አሁን ላይ ወደ 55 ከመቶ የደረሰ ሲሆን በቀጣዮቹ ሁለት አመታት ጊዜ ዉስጥ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ይገኛል፡፡ የወሰን ማስከበር ፣ የግብዓት አቅርቦት፣ በጀት እጥረትና መሰል ችግሮች ፕሮጀክቱን እያጓተቱ ያሉ ችግሮች ሲሆኑ በቀጣይ እነዚህ ችግሮች ከተቀረፉ ለማጠናቀቅ በተያዘለት የእቅድ ሰሌዳ መሰረት እንደሚጠናቀቅ ፕሮጀክቱን እየመሩ ያሉ ባለሙያዎች ተናግረዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ ...

የአብክመ ውሃና ኢነርጅ ቢሮ ከዞን ውሃና ኢነርጅ መምሪያ ሃላፊዎች ጋር በበጀት አመቱ በቀሩት ወራት ትኩረት ተሰጥቷቸው በሚከናወኑ ተግባራት ዙሪያ ውይይት እያካሄደ ነው።

የአብክመ ውሃና ኢነርጅ ቢሮ ከዞን ውሃና ኢነርጅ መምሪያ ሃላፊዎች ጋር በበጀት አመቱ በቀሩት ወራት ትኩረት ተሰጥቷቸው በሚከናወኑ ተግባራት ዙሪያ ውይይት እያካሄደ ነው። አሁን እየተካሄደ ያለውን ውይይት የቢሮው ሃላፊ ዶ/ር ማማሩ አያሌው እየመሩት ሲሆን የመልካም አስተዳደር ችግር የሆኑ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች፣ በክልሉ ምክር ቤት የተነሱ ጥያቄዎች ፣የመመሪያዎች ተፈፃሚነት፣ የባዮ ጋዝ ግንባታ ያለበት ደረጃ፣ የእቅድ አፈፃፀሞችና መሰል ጉዳዮች ላይ ውይይት በማድረግ የጋራ መግባባት ላይ ይደረሳል ተብሎ ይጠበቃል:: ዝርዝር መረጃውን ከውይይቱ መጠናቀቅ በኋላ እናቀርባለን።

ተጨማሪ ያንብቡ ...

የደሴ ከተማ አስተዳደር የመጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽህፈት ቤት በዉሃ አቅርቦት ዙሪያ ዉይይት አደረገ

N4የደሴ ከተማ አስተዳደር የመጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽህፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ወርቁ አሞኜ በ2011 ዓመተ ምህረት በሁሉም ተቋሞቻችን በድግግሞሽ 4ሺህ 573 ስዓት መብራት በመጥፋቱ ምክንያት 435ሺህ 600 ሜትር ኩብ ውሃ ሳይመረት ቀርቷል፤ በገንዘብ ሲተመንም በዝቅተኛው 2 ሚሊዮን 461ሺህ 140 ብር መስሪያ ቤቱ ገቢ ማጣቱንና በሥራ ላይ ያጋጠማቸው ችግሮችም የኔት ወርክ መቆራረጥ ችግር፣ የፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ ቦታ ችግር አለመፈታት፣በደርቅ ቆሻሻ ክፍያ አፈፃፀምና አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ያለው ችግር፤ ለገጠር ቀበሌ ኗሪዎች የንጹህ መጠጥ ዉሃ ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል በጀት በክልሉና በከተማ አስተዳደሩ አለመሰጠቱ፤ በዉሃ ምርትና በደንበኞች አዳጊ ፍላጎት መካካል ሰፊ ልዩነት መኖሩ የሚሉት ዋና ዋናዎቹ እንደሆኑና አመራሩም በቀጣይ በጋራ ተቀናጅቶ ትኩረት በመስጠት እንዲሰራ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ ...

የአብክመ ዉኃና ኢነርጂ ቢሮ እና አለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ /ICRC/ የላል ይበላ ከተማ መጠጥ ዉሃ ፕሮጀክትን ወደ ሶላር ለመቀየር የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ

አሸባሪዉ የህዉሃት ወረራ ሃይል በላል ይበላ ከተማ ወረራ ፈጽሞ ጉዳትና ዝርፊያ አድርሶ ከወጣ በኃላ ከተማዉ ከዋናዉ የኤሌክትሪክ መስመር እየገኘ የነበረዉ ሃይል መቋረጡ ይታወቃል፡፡ ይህንን ተከትሎም ለከተማዉ ህብረተሰብ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘዉ ንጹህ መጠጥ ዉሃ ተቋም በዲዝል ሃይል እየሰራ ለህብረተሰቡ ዉሃ እያቀረበ ቢሆንም የነዳጅ ፍጆታዉ ከፍተኛ በመሆኑ ለህብረተሰቡ የተሟላ አገልግሎት መስጠት አልተቻለም፡፡ ስለሆነም የተለያዩ አማራጮችን መጠቀም አስፈላጊ ሁኖ ተገኝቷል፡፡ በዚህ ረገድ እንደነዚህ አይነት ተቋማትን እየደገፉ ከሚገኙት መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት መካከል አለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ /ICRC/ አንዱና ዋናዉ ነዉ፡፡ በህግ ማስከበር ሆነ በህልዉና ዘመቻዉ ወቅት በዘርፉ ከፍተኛ ድጋፍ ካደረጉትና እያደረጉ ካሉ መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት መካካል አለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ /ICRC/ በዋናነት የሚጠቀስ ነዉ፡፡ ይህንን ድጋፉን አሁንም አጠናክሮ በመቀጠል በሁለት ፌዝ በመክፈል የላል ይበላ ከተማ የዉሃ አቅርቦትን በሶላር ፓምፕ ለማድረግ ከቢሮዉ ጋር የስምምነት ፊርማ ተፈራርሟል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ ...

አስተያየትዎን ይስጡን

Logoየአብክመ ዉሃ፣መስኖና ኢነርጂ ልማት ቢሮ አዲስ ድረ-ገፅ እያስለማ ይገኛል። ይህን የምታዩት ድረ-ገፅ የተሻለ ለማድረግ የእርሶ ሃሳብና አስተያየት በጣም ጠቃሚ ነው። ስለዚህ የሚታዮትን ሁሉ አስተያይት ይስጡን። ለሚሰጡን አስተያየት ምስጋናችንን በቅድሚያ እናቀርባለን።

 

ተጨማሪ ያንብቡ ...

መጪ ዝግጅቶች

No events

ጎብኚዎችን ቆጣሪ

276641
ዛሬ
ትናንት
በዚህ ሳምንት
ባለፈው ሳምንት
በዚህ ወር
ባለፈው ወር
ጠቅላላ
43
44
409
275575
1696
4825
276641