የአብክመ ውሃ መስኖና ኢነርጂ ልማት ቢሮ በመጠጥ ውሃ አቅርቦት እና በመስኖ ግንባታ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያካሄደ ነው

N1ስብሰባዉን በንግግር የከፈቱት የአብክመ ውሃ መስኖና ኢነርጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ማማሩ አያሌዉ እንደገለጹት በአሁኑ ስአት በመጠጥ ውሃ አቅርቦቱ እና በመስኖ ግንባታው ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ከፍተኛ ጥረትና አዳዲስ አሰራሮችን በመቅረጽ መተግበር ካልቻልን ወደፊት የሚመጣውን የክልሉን ህዝብ የመጠጥ ውሃ ፍላጎት በአግባቡ ተደራሽ ማድረግ የሚያዳግተን መሆኑንና በመስኖ ልማቱ ዘርፍም ከዚህ ቀደም 100 ሽህ ሄክታር መሬት የሚያለሙ በርካታ ፕሮጀክቶችን መገንባት ብንችልም ከዲዛይን ጀምሮ እስከ ግንባታ ጥራት ድረስ ከፍተኛ ችግር እያጋጠማቸው ስለሆነ በእቅዳችን መሰረት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ እያደረግን እንዳልሆነ ተረድተን በቀጣይ እዚህ ውይይት ላይ እየተሳተፍን ያለን አካላት በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመቅረፍ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ እናደርግ ዘንድ ከወትሮው በተለየ ተቀናጅተን መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡


የአብክመ ርዕሰ መስተዳድር የመሰረተ ልማት አማካሪ አቶ ደሳለኝ አስራደ ዉይይቱን በክብር እንግድነት ሲከፍቱ እንደገለጹት በክልላችን በሚገነቡ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚሰተዋሉ ችግሮች አሉ ፤ ከዚህ ጋር በተያያዘ ለክልሉ ህዝብ አገልግሎት ይሰጡ ዘንድ ታስቦ ከሚገነቡ የንጹህ መጠጥ ውሃ ተቋማት ወስደን ስንመለከት በርካታ ግንባታዎች ለብልሽት እየተዳረጉ እንዳሉ ይታወቃል፡፡ ከዚህም በላይ የግንባታ መጓተት፣ የጥራት መጓደልና ሌሎች ተያያዥ ችግሮች በህብረተሰቡ ተጠቃሚነት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እየፈጠሩ ይገኛሉ፡፡ በመሆኑም የእነዚህን ችግሮች መነስዔ በጋራ በመምከር መፍትሄ መሰጠት አለበት ብለዋል፡፡ ለተገነቡ የመጠጥ ዉሃና የመስኖ ግንባታዎች ላይም አስፈላጊውን እንክብካቤና ጥበቃ ልናደርግላቸው ይገባል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ለዉይይት መነሻ የሚሆን ሪፖርት የአማራ ዲዛይን፣ ቁጥጥርና ሱፐርቪዥን ስራዎች ድርጅት ያቀረበ ሲሆን የዉሃ፣መስኖና ኢነርጂ ልማት ቢሮ ምክትል ሃላፊዎች አቶ ይመር ሃብቴና አቶ መለሰ ስንታየሁ በመጠጥና መስኖ ግንባታ ዘርፎች እያጋጠሙ ያሉ የመልካም አስተዳዳር ችግሮች በፕሮጀክት ደረጃ አቅርበዋል፡፡ በነዚህ የዉይይት መነሻ ሪፖርቶች አሁን ላይ ዉይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ በዚህ መድረክ የዞን ዋና አስተዳዳሪዎች፣ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ስራ አስፈጻሚዎችና የስራ ሃላፊዎች የዉሃ፣መስኖና ኢነርጂ ልማት መምሪያ ሃላፊዎች፣ የቢሮዉ ሃላፊዎችና ስራ አመራር አባላት እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸዉ አካላት እየተሳተፉበት ይገኛል፡፡ ዉይይቱ በተለያዩ አጀንዳዎች ዙሪያ በመምከር ዉሳኔዎች ተላልፈዉ በነገዉ እለት የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡

 

መጪ ዝግጅቶች

No events

ጎብኚዎችን ቆጣሪ

353870
ዛሬ
ትናንት
በዚህ ሳምንት
ባለፈው ሳምንት
በዚህ ወር
ባለፈው ወር
ጠቅላላ
340
348
1656
348386
14600
59172
353870