ዶ/ር ማማሩ አያሌዉ ሞገስ
የአብክመ ዉሃ፣መስኖና ኢነርጂ ልማት ቢሮ ሃላፊ
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ልማት ቢሮ የክልሉን የውሃ ሃብት ማስተዳደር፣ ንጹህ የመጠጥ ውሃ ማቅረብ፣ ከአነስተኛ እስከ መካከለኛ ደረጃ ያሉ የመስኖ አውታሮችን በመገንባት ለተጠቃሚው ህብረተሰብ ማስተላለፍና የአማራጭ ኢነርጂ ቴክኖሎጂዎችን በማስተዋወቅና በማቅረብ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ ከክልሉ መንግስት የተሰጠው ተግባርና ሃላፊነት በመሆኑ ይህን ተግባርና ኃላፊነት ለመወጣት የሚያስችል ሰፊ ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡
በሁለተኛዉ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ሽፋን በገጠር ሁሉም አርሶ አደር ከሚኖርበት አካባቢ ከ1 ኪ/ሜ በላይ ሳይጓዝ 25 ሊትር ዉሃ በቀን ለእያንዳንዱ ሰው፤ በከተማ የህዝብ ቁጥራቸዉ ከ20,000 እስከ 999,999 ህዝብ ለሚኖርባቸዉ የክልላችን ከተሞች ከ50 እስከ 80 ሊትር ዉሃ በቀን ለሰዉ ለማዳረስና የህዝብ ቁጥራቸዉ ከ20,000 በታች ለሆኑ የክልላችን ከተሞች በ250 ሜትር ርቀት 40 ሊትር ዉሃ በቀን ለሰዉ ለማድረስ የተቀመጠዉን አዲስ ስታንዳርድ መሰረት በማድረግ የተጣለዉን ግብ ለማሳካት ሰፊ ርብርብ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
በዚህም መሰረት ከላይ በተቀመጠዉ ስታንዳርድ በዕትዕ-2 መጀመሪያ የንጹህ መጠጥ ዉሃ ሽፋናችን በገጠር 53.46% በከተማ 54% እንደ ክልል 53.54% ላይ የደረሰ ሲሆን ከዚህ በመነሳት በአምስት ዓመት የተቀመጠዉን ግብ ለማሳካት ከፍተኛ ስራ ተሰርቶ በከተማም ሆነ በገጠር የንጹህ መጠጥ ዉሃ ሽፋኑን ከፍ ማድረግ ተችሏል፡፡
Read more ...የጎንደር ከተማ ህብረተሰብን በዘላቂነት የንጹህ መጠጥ ዉሃ ተደራሽ ለማድረግ ከመገጭ መስኖ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ጋር አቀናጅት እየተሰራ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ይህ ፕሮጀክት የደረሰበትን ደረጃና አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ ለመመልከት የአብክመ ዉሃና ኢነርጂ ቢሮ ሰራተኞችና አመራሮች ጉብኝት አድገዋል፡፡ በዚህም መሰረት ፕሮጀክቱ አሁን ላይ ወደ 55 ከመቶ የደረሰ ሲሆን በቀጣዮቹ ሁለት አመታት ጊዜ ዉስጥ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ይገኛል፡፡ የወሰን ማስከበር ፣ የግብዓት አቅርቦት፣ በጀት እጥረትና መሰል ችግሮች ፕሮጀክቱን እያጓተቱ ያሉ ችግሮች ሲሆኑ በቀጣይ እነዚህ ችግሮች ከተቀረፉ ለማጠናቀቅ በተያዘለት የእቅድ ሰሌዳ መሰረት እንደሚጠናቀቅ ፕሮጀክቱን እየመሩ ያሉ ባለሙያዎች ተናግረዋል፡፡
የአብክመ ውሃና ኢነርጅ ቢሮ ከዞን ውሃና ኢነርጅ መምሪያ ሃላፊዎች ጋር በበጀት አመቱ በቀሩት ወራት ትኩረት ተሰጥቷቸው በሚከናወኑ ተግባራት ዙሪያ ውይይት እያካሄደ ነው። አሁን እየተካሄደ ያለውን ውይይት የቢሮው ሃላፊ ዶ/ር ማማሩ አያሌው እየመሩት ሲሆን የመልካም አስተዳደር ችግር የሆኑ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች፣ በክልሉ ምክር ቤት የተነሱ ጥያቄዎች ፣የመመሪያዎች ተፈፃሚነት፣ የባዮ ጋዝ ግንባታ ያለበት ደረጃ፣ የእቅድ አፈፃፀሞችና መሰል ጉዳዮች ላይ ውይይት በማድረግ የጋራ መግባባት ላይ ይደረሳል ተብሎ ይጠበቃል:: ዝርዝር መረጃውን ከውይይቱ መጠናቀቅ በኋላ እናቀርባለን።
አሸባሪዉ የህዉሃት ወረራ ሃይል በላል ይበላ ከተማ ወረራ ፈጽሞ ጉዳትና ዝርፊያ አድርሶ ከወጣ በኃላ ከተማዉ ከዋናዉ የኤሌክትሪክ መስመር እየገኘ የነበረዉ ሃይል መቋረጡ ይታወቃል፡፡ ይህንን ተከትሎም ለከተማዉ ህብረተሰብ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘዉ ንጹህ መጠጥ ዉሃ ተቋም በዲዝል ሃይል እየሰራ ለህብረተሰቡ ዉሃ እያቀረበ ቢሆንም የነዳጅ ፍጆታዉ ከፍተኛ በመሆኑ ለህብረተሰቡ የተሟላ አገልግሎት መስጠት አልተቻለም፡፡ ስለሆነም የተለያዩ አማራጮችን መጠቀም አስፈላጊ ሁኖ ተገኝቷል፡፡ በዚህ ረገድ እንደነዚህ አይነት ተቋማትን እየደገፉ ከሚገኙት መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት መካከል አለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ /ICRC/ አንዱና ዋናዉ ነዉ፡፡ በህግ ማስከበር ሆነ በህልዉና ዘመቻዉ ወቅት በዘርፉ ከፍተኛ ድጋፍ ካደረጉትና እያደረጉ ካሉ መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት መካካል አለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ /ICRC/ በዋናነት የሚጠቀስ ነዉ፡፡ ይህንን ድጋፉን አሁንም አጠናክሮ በመቀጠል በሁለት ፌዝ በመክፈል የላል ይበላ ከተማ የዉሃ አቅርቦትን በሶላር ፓምፕ ለማድረግ ከቢሮዉ ጋር የስምምነት ፊርማ ተፈራርሟል፡፡
የደሴ ከተማ አስተዳደር የመጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽህፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ወርቁ አሞኜ በ2011 ዓመተ ምህረት በሁሉም ተቋሞቻችን በድግግሞሽ 4ሺህ 573 ስዓት መብራት በመጥፋቱ ምክንያት 435ሺህ 600 ሜትር ኩብ ውሃ ሳይመረት ቀርቷል፤ በገንዘብ ሲተመንም በዝቅተኛው 2 ሚሊዮን 461ሺህ 140 ብር መስሪያ ቤቱ ገቢ ማጣቱንና በሥራ ላይ ያጋጠማቸው ችግሮችም የኔት ወርክ መቆራረጥ ችግር፣ የፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ ቦታ ችግር አለመፈታት፣በደርቅ ቆሻሻ ክፍያ አፈፃፀምና አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ያለው ችግር፤ ለገጠር ቀበሌ ኗሪዎች የንጹህ መጠጥ ዉሃ ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል በጀት በክልሉና በከተማ አስተዳደሩ አለመሰጠቱ፤ በዉሃ ምርትና በደንበኞች አዳጊ ፍላጎት መካካል ሰፊ ልዩነት መኖሩ የሚሉት ዋና ዋናዎቹ እንደሆኑና አመራሩም በቀጣይ በጋራ ተቀናጅቶ ትኩረት በመስጠት እንዲሰራ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡