የአብክመ ዉሃ፣መስኖና ኢነርጂ ልማት ቢሮ

የአብክመ ዉሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ልማት ቢሮ አሁን የያዘዉን ስያሜና ቅርጽ ከመያዙ በፊት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት የአስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባራት ለመወሰን ባወጣዉ አዋጅ አዋጅ ቁጥር 4/1988 ዓ.ም መሰረት  የአብክመ ዉሃ፣ ማእድንና ኢነርጂ ሃብት ልማት ቢሮ በሚል ተቋቁሞ ነበር፡፡ ከዚያም የማዕንና የኢነረጂ ዘርፉን ከዉሃ ቢሮ በመነጠል በ1997 ዓ.ም በአዋጅ ቁጥር 99/1997 የዉሃ ሃብት ልማት ቢሮ ተብሎ የራሱ ተግባርና ሃላፊነቶች ተሰጥቶት ቆይቷል፡፡ ከዚያም እስከ 2008 ዓ.ም ድረስ በዚህ ስያሜ ከቀጠለ በኋላ በ2008 ዓ.ም በክልሉ መንግስት ምክር ቤት  ባወጣዉ አዋጅ ቁጥር 230/2008 ዓ.ም በአማራ ክልላዊ መንግስት የተሻሻለዉ የአስፈጻሚ አካላት ማቋቋሚያ፣ ማደራጃና ስልጣንና ተግባራት መወሰኛ አዋጅ መሰረት በአዲስ መልክ አሁን የያዘዉን ስያሜ፣ ቅርጽና ይዘት በመያዝ ተቋቋመ - አብክመ ዉሃ፣መስኖና ኢነርጂ ልማት ቢሮ   

ቢሮዉ ለክልሉ ፕሬዚዳንት ተጠሪ የሆነ አንድ የቢሮ ሃላፊ እና  ሶስት ምክትል ቢሮ ሃላፊዎች አሉት፡፡ እነዚህ ምክትል ቢሮ ሃላፊዎች ተጠሪነታቸዉ ለቢሮ ሃላፊዉ ሁኖ የመጠጥ ዉሃ ዘርፍ፣ የመስኖ ዘርፍ እና ኢነርጂ ዘርፍ ተብለዉ የስራ ድልድል ተሰጥቷቸዉ እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ በቢሮ ሃላፊዉና በእነዚህ የስራ ዘርፎች ስር 12 ዳይሬክቶሬቶች ተቋቁመዉ የሚጠበቅባቸዉን ተግባርና ሃላፊነቶች እየተወጡ ይገኛሉ፡፡ እነርሱም፡-

  1. የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
  2. የመጠጥ ዉሃ አቅርቦት ዳይሬክቶሬት
  3. የመስኖ ጥናት፣ዲዘይንና ግንባታ ክትትል ዳይሬክቶሬት
  4. የዉሃ ሃብትና ተቋማት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
  5. የዉሃ ተቋማት ግንባታ ግብዓት አቅርቦት ዳይሬክቶሬት
  6. የባዮ-ኢነርጂ ምንጮች ቴክኖሎጅ ማስፋፊያ ዳይሬክቶሬት
  7. የኤሌክትሪክ ምንጮች ቴክኖሎጅ ማስፋፊያ ዳይሬክቶሬት
  8. የሰዉ ሃብት ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት
  9. የዉስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት
  10. ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
  11. የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት
  12. የእቅድ ዝግጅት፣ክትትልና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት

ሲሆኑ ከዚህ በተጨማሪ ራሳቸዉን ችለዉ በባለሙያ ደረጃ የሚመሩ መደቦችም ተቋቁመዋል፡፡  እነርሱም

  1. የህግ አገልግሎት
  2. የኤች አይቪ ኤድስና ስርዓተ ጾታ
  3. የአገልግሎት አሰጣጥና ቅሬታ ሰሚ ይገኙበታል፡፡

ከላይ ከተጠቀሱት ዳይሬክቶሬቶች መካከል በተለይም  በግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት /3/፣ በመጠጥ ዉሃ አቅርቦት ዳይሬክቶሬት /3/፣ በመስኖ ጥናት፣ዲዛይንና ግንባታ ክትትል ዳይሬክቶሬት /2/ እና በዉሃ ሃብትና ተቋማት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት /3/  በአጠቃላይ 11 ቡድኖች ተቋቁመዋል፡፡

ከመደበኛ ሲቪል ሰርቪስ መዋቅር በተጨማሪ በቢሮዉ በተለያዩ ዘርፎች የሚሰሩ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ፕሮጀክቶች በዋናነት የቢሮዉን ተልዕኮ በአግባቡ እንዲወጣ ለማድረግ ገንዘብና የሰዉ ሃይል በመመደብ ከቢሮዉ ጋር የሚሰሩ ናቸዉ፡፡ እነዚህ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች፡-

  1. ሁለተኛዉ የአንድ ዋሽ ማስተባበሪያ ዩኒት - መጠጥ ዉሃ ላይ የሚሰራ
  2. ሁለተኛዉ የግብርና እድገት ፕሮግራም - መስኖ ግንባታ ላይ የሚሰራ
  3. ማህበረሰብ መር የተፋጠነ የዉሃ፣ ሳኒቴሽንና ሃይጅን ፕሮግራም - መጠጥ ዉሃ ላይ የሚሰራ
  4. ባዮ-ጋዝ ማስተባበሪያ ዩኒት - በኢነርጂ በተለይም ባዮጋዝ ግንባታ ላይ የሚሰራ
  5. ዩኒሴፍ - መጠጥ ዉሃ ላይ የሚሰራ

ቢሮዉ በአስር ዞኖች የዞን ዉሃ፣መስኖና ኢነርጂ ልማት መምሪያዎች ተቋቁመዉ በቅርብ ርቀት ቢሮዉን ወክለዉ የየዞናቸዉን ህብረተሰብ ይደግፋሉ፡፡ ሁለቱ በቅርብ የተቋቋሙ የሰሜን ጎንደርና የምዕራብ ጎንደር ዞኖች በግብርና መምሪያ ስራ የዉሃ የስራ ሂደት ተቋቁሞ እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ በክልሉ በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች የዉሃና ኢነርጂ ልማት ጽ/ቤት ተቋቁሟል፡፡

መጪ ዝግጅቶች

No events

ጎብኚዎችን ቆጣሪ

276631
ዛሬ
ትናንት
በዚህ ሳምንት
ባለፈው ሳምንት
በዚህ ወር
ባለፈው ወር
ጠቅላላ
33
44
399
275575
1686
4825
276631